የስሜት ብስለት (Emotional Intelegence) ምንድ ነዉ?

የስሜት ብስለት ማለት የራስን ስሜት የመምራትና በሌሎች ስሜት ላይ በጎ ተፅዕኖ የማድረግ ችሎታ ነው። ይህም ማለት ሰዎች የራሳቸውን ስሜት መመልከት፣ መቆጣጠርና መመራት መቻልን እንዲሁም የሌሎችን ስሜት መረዳትና አወንታዊ ተፅዕኖ መፍጠር መቻልን ያካትታል።
የስሜት ብስለት የተሟላለት ሰው በየጊዜው በስሜቱ የሚናወጥ ባለመሆኑና የራሱን ስሜት መረዳትና መምራት የሚችል በመሆኑ አጥርቶ ማሰብ ይችላል፤ በአስቸጋር ሁኔታዎች ውስጥም ሆኖ የሚፈፅማቸው ድርጊቶችና የሚወስናቸው ውሳኔዎች ከስሜት ግፊት የፀዱና ምክንያታዊነት ያላቸው ስለሚሆኑ ነገሮች ከቁጥጥሩ ውጪ አይሆኑም። በዚህም ለችግሮች አማራጫዊ መፍትሄዎችን መመልከት ይችላል። በህይወት ውጣ ውረድ ውስጥ የሚገጥሙት ግራ መጋባቶችና መገለሎች ሳይጥሉት ተሻግሮ ማለፍ የችላል። ከሌሎች ጋር በሚያደርጋቸው ግንኙነቶች ጊዜ አቀራረቡ መልካም ስሜትን የተላበሰ በመሆኑ በሚገባ መግባባት ይችላል በሌሎች ስሜት ላይም በጎ ተፅዕኖ በማሳረፍ ዕምነት እንዲጥሉበት የማድረግ ጉልበት አለው። በዚህም መልካም መሪ መሆን ይችላል።

ምንጭ: ስሜትና አዕምሮ መፅሀፍ/ከተማ አድማሱ

1 Comment

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s