አቶ ተመስገን ጥሩነህ የኢትዮ ቴሌኮምና የኢትዮ ኤሌክትሪክ ኃይል ኃላፊዎችን በተለያዩ ዞኖች እያደረጓቸው ያሉትን ጉብኝቶች

የተከበሩ አቶ ተመስገን ጥሩነህ በተለያዩ ዞኖች እያደረጓቸው ያሉትን ጉብኝቶች የኢትዮቴሌኮምና የኢትዮ ኤሌክትሪክ ኃይል ኃላፊዎችን ይዘው መጎብኘታቸው በጣም ጥሩ ተግባር ነው። የመንገዶች ባለሥልጣን ኃላፊውንም ቢጨምሩ የበለጠ ጥሩ ነበር የሚል ሐሳብ አለኝ።
ክቡር ርእሰ መስተዳድር ወደ ደቡብ ወሎ በሚያደርጉት ጉብኝት በተለይ በኤሌክትሪክ ኃይል ይዘው በመሄድ ከአዋሽ-ኮምቦልቻ ለተዘረጋው የባቡር መስመር ስለምን ኤሌክትሪክ ማቅረብ እንዳልፈለጉ ይጠይቁልን። ተሠርቶ ለተጠናቀቀ የኤሌክትሪክ ሥራ ርክክብ ለማድረግ እንኳን ኃይል መልቀቅ አልተፈለገም። ባቡሮች ተገዝተው ድሬዳዋ እና ጂቡቲ ከተገተሩ ዓመት አልፏቸዋል። ሐዲዱም ከተጠናቀቀ ዓመት አልፎታል። ለፕሮጀክቱ የዋለው ብድር ወለዱ በአናት በአናት ይጨምራል። ርክክብ ባለመደረጉ የአገር ወጭ እየጨመረ ነው። ከእዚያ በላይ ደግሞ፣ የተወሰኑ የአፋር ክልል ከተሞችን ጨምሮ ከአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ሸዋሮቢት፣ አጣዬ፣ ማጀቴና መኮይ፣ በኦሮሞ አስተዳደር ዞን ለሚገኙ ሰንበቴና ከሚሴ ከተሞች ተጨማሪ ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴ እንዲኖር ያግዛል።
በተለይ በተለይ ለኮምቦልቻ ከተማ እና ለአካባቢው ሕዝብ ፋይዳው ከፍተኛ ነው። ደረቅ ወደብ አለ። የኢንዱስትሪ ፓርክ አለ። በርካታ ፋብሪካዎች አሉ። የባቡሩ መጀመር፣ ጥናቶች እንደሚያሳዩት ወደ ወደብ የሚደረገውን የጭነት የትራንስፖርት ወጭ በግማሽ ይቀንሳል። ይሄ ደግሞ የባለሃብቶችን ተወዳዳሪነት ከመጨመሩም በላይ ተጨማሪ ባለሃብቶች በአካባቢው ኢንቨስት እንዲያደርጉ ያግዛል።
በመሆኑም፣ የኤሌክትሪክ ኃይል ለመስጠት ፈቃደኛ ለምን እንዳልሆነ እንዲሁም እየደረሰ ያለውን ኢኮኖሚያዊ በደል መላ ይበሉልን።

Wubishet Mulat

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s