ኢትዮጵያን ለማዳን አማራን ማዳን! (አቶ መኮንን ዶያሞ)

 1. አማራ ላይ የሚፈፀሙ ጥቃቶች ጣሊያን ኢትዮጵያን ለማጥፋት ከነደፈው ስትራቴጂ የተቀዱ ናቸው፤ ጣሊያን ኢትዮጵያን ለማጥፋት አማራን ማጥፋት የሚል አቋም ነበረው፤ ዛሬም ኢትዬጵያን ለማፍረስ የሚሞክሩ ሃይሎች የጣሊያንን አካሄድ ነው የኮረጁት።
 2. ኢትዮጵያን ለማዳን አማራን ማዳን ይገባል፤ ምክንያቱም አማራ ላይ የሚያነጣጥር ጥቃት በመላው ሃገሪቱ ተሰራጭቶ የሚኖረውን ከተማ መስራችና የስልጣኔ ምንጭ የሆነውን ህዝብ ለማጥፋት ስለሆነ ነው።
 3. የአማራ ህዝብ ቁጥር አሁን የአማራ ክልል ተብሎ በሚጠራው ክልል ውስጥ ከሚኖረው የአማራ ቁጥር ይበልጣል፤ ይህም ብቻ አይደለም አጠቃላይ የኦሮሞ ህዝብ ቁጥር ከአማራ ክልል ውጪ ከሚኖረው የአማራ ህዝብ ቁጥርም ያንሳል።
 4. ዛሬ የኦሮሞ ህዝብ ቁጥር ይበልጣል ተብሎ እንዲታሰብ የተደረገው የወያኔ ስራ ሲሆን ፈፅሞ ውሽት ነው፤ ሸዋ ውስጥ ስንመጣ የምናገኘው ሰላሌ ብቻ ነበር። ወሎ ስንሄድ አንድ ወረዳ ነበር፤ ከዛ ውጪ በመላ ሃገሪቱ ብንመለከት የአማራ ህዝብ በየከተማ በየገጠሩ majority ነው።
 5. ኦነግ የኢትዮጵያ ጠላቶች tool (መጠቀሚያ) ነው፤ ዋና አላማውም በያካባቢው አንዱን ከሌላው እያጋጨና እየለያዬ ራሱን ወዳጅ አድርጎ በማቅረብ አጋዥ በማግኘት የሳለውን ህገ ወጥ የወረራ ካርታ እውን ማድረግ ነው።
 6. ኦነግ እኮ ጋሞ ጎፋን ከሞላ ጎደል የያዘ፣ ሲዳማን በክልልነት ጥያቄ ነጥሎ ወደራሱ ለመጠቅለል እየሞከረ ያለ፣ ከፋንና ጌዶን አፈንልቅሎ በቁጥጥሩ ስር በከፊል ያደረገ፣ ጉራጌን በገንዘብም በፕሮፓጋንዳም ለመጠቅለል እየሞከረ ያለ ሃይል ነው። ቅርብ ጊዜ “የጉራጌ አባ ገዳ ባህል” የሚል ነገር ሰምተናል።
 7. ለምን የኦሮምያ ክልል እንደሚባል አላውቅም፤ ኦሮምያ ተብሎ የሚጠራውን አካባቢ ብናይ እኮ ናዝሬት ብዙሃኑ አማራ ነው፤ ደብረ ዘይት አማራ ነው፤ ወለጋን ብናይ የጃም ክፍለ ሃገር አካል የነበረ ነው፤ አርሲና ባሌ አብዛኛው ነዋሪ አማራና ሰፊው ብዙሃኑ የኢትዮጵያ ህዝብ ነው የሚኖርበት፤ ይህ ክልል በፍፁም የኦሮምያ ክልል መባል የለበትም ነበር።
 8. #ኤጄቶ የሚባለው ቡድን ከሲዳማ ህዝብና ባህል ውጪ ነው፤ ኦነግ ሲዳማን ለመጠቅለል ሲፈልግ ያሰለጠነው ጋጠወጥ ቡድን ነው፤ እቅዱ የኦነግን ፀረ አማራ እንቅስቃሴ ከሲዳማ ህዝብ ጋር ለማነካካት ነበር፤ የተፈጠረውን ችግርም ስንመለከት በአብዛኛው አማራንና የኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያንን ኢላማ ውስጥ ያስገባ ነው፤ ግን የሲዳማ ህዝብ አልተባበረም፤ ምክንያቱም የሲዳማ ህዝብ ከአማራ ህዝብ ጋር ቤተሰብ ነን ብሎ ስለሚያስብ ነው።
 9. #Ejetto የሲዳምኛ ቃል አይደለም፤ በሲዳምኛ ትክክለኛ ቃሉ አጋቶ ሲሆን ትክክለኛ ስሙም # መርገጫ ማለት ነው። ይህ ቡድን ከስሙ ጀምሮ ከሲዳማ ህዝብ ጋር ምንም ግንኙነት የለውም።
 10. ኢትዮጵያን ለማዳን የሚፈልግ ሰው አማራ የጀመረውን ትግል መደገፍና አጋርነቱን ማሳየት አለበት። የሲዳማ ህዝብ አጋርነቱን ለማሳየት ዝግጁ ነው፤ የወላይታ ዝህብም አጋርነቱን እንደገለፀ መረጃው አለኝ፤ የጋሞጎፋ ህዝብ ለአማራ ህዝብ ያለው ድጋፍ የተለየ ነው፤ የከፋውም የጉራጌውም እንዲሁ! አሁንም ቢሆን ከአማራ ጎን ተሰልፈን ነው ኢትዮጵያን ማዳን የምንፈልገው።
 11. እኔ ጫካ ውስጥ ነው የተወለድኩት፤ ከጫካ ወጥተን ከተማ ውስጥ መኖር የጀመርነው፣ ሀ ሁ ተምረን ማንበብና መፃፍ የጀመርነው፣ .. ሃገር መስራቹ የአማራ ህዝብ በመሰረተው ከተማ ውስጥ ነው፤ ዛሬ ካሉት ከተማዎች ውስጥ አማራ ያልመሰረታቸው ከተሞች የሉም።

በአለባቸው ግርማ

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s