በኦሮሞ ብሔርተኞች የተወረሰው የመንዙ አማራ- አትሌት አበበ ቢቂላ

የኦሮሞ ብሔርተኛነት እንቅስቃሴ ስለ እኩልነትና ዲሞክራሲ የሚደረግ ትግል ሳይሆን ሰማዩንም ምድሩንም «ኬኛ» የሚል የወረራና የመውረስ መንፈስ የተጠናወተው የዝቅተኝነት ፖለቲካ ነው። አዲስ አበባን ለመውረስ እያደረጉት ያለው ማሰፍሰፍ የዚህ የወረራና የመውረስ መንፈስ የተጠናወተው ፖለቲካቸው አንድ አካል ነው።

ከደጃዝማች በላይ ዘለቀ ላቀው አገኜሁ ቀጥሎ የኦሮሞ ብሔርተኞች የመውረርና የመውረስ ፖለቲካ ሰለባ ከሆኑት ታላላቅ ሰዎች መካከል ጀግናው አትሌት ሻምበል አበበ ቢቂላ አንዱ ነው። ታላቁ አትሌት ሻምበል አበበ ቢቂላ ሰላሌ ላይ በዐቢይ አሕመድ ተመርቆ በተከፈተው «የሰላሌ ኦሮሞ የባሕል ማዕከል» ውስጥ ተወርሶ በኦሮሞ ብሔርተኞች ኦሮሞ ተደርጓል። ለኦሮሞ ብሔርተኞች ሰውንም ይሁን ቤትን፤ ምድሩንም ይሁን ሰማዩን ለመውረስና ለመውረር እውነት፣ ታሪክና እውቀት አያግዳቸውም። ይህም በመሆኑ በእናቱም በአባቱም የመንዝ አማራ የሆነውን ሻምበል አበበ ቢቂላን ኦሮሞ አድርገው ወርሰውታል።

የኦሮሞ ብሔርተኞች ታላቁን ሰው አበበ ቢቄላን ወርሰው ኦሮሞ ሲያደርጉት የአበበ ቢቄላ የቤተሰብ ታሪክ አላስጨነቃቸውም። ፖለቲካቸው የዝቅተኛነት ደዌ የተጠናወተው የመውረርና የመውረስ በሽታ ስለሆነ ትልቅ የተባለን ሰው ኦሮሞ ካላደረጉ ሰው ሆነው የሚቆሙ አይመስላቸውም። መንግሥት ነኝ በሚለው አካል ተመርቆ በተከፈተው የባሕል ማዕከል ውስጥ ኦሮሞ ተደርገው ስለቀረቡት ሰዎች ማንነትና ታሪክ በባለሞያ ለማስጠናት ሙዝ የመላጥ ያህል እንኳ ሙከራ አላደረገም፤ እንዲደረግም አይፈልግም። የማጣራት ሙከራ የማይደረገውም እውነቱ/ውጤቱ የኦሮሞ ብሔርተኞች የማይፈልጉት ሆኖ ስለሚገኝ ብቻ ነው።

አበበ ቢቄላን ኦሮሞ የማድረጉን ዘመቻ የጀመረው ኢንዲያና ዩኒቨርሲቲ እንደሚያስተምር ፕሮፋይሉ የሚያሳየው ዶክተር አሰፋ ተፈራ ድሪባ የተባለ ሰው ነው። ዶክተር አሰፋ ድሪባ ” THE FOLKLORE OF IDENTITY THEFT: Restorying Abebe Biqila” በሚል እ.ኤ.አ. በ2012 ጽፎ advocacy4oromia.org በሚል ድረ ገጽ ባሳተመው ጽሑፍ አበበ ቢቄላ ኦሮሞ እንደሆነና የተነጠቀው የኦሮሞ ማንነቱ መመለስ እንዳለበት ጥሪ ያስተላልፋል። በመሰረቱ ማንነት የማንነቱ ባለቤት የሚወስነው ብያኔ እንጂ ዶክተር አሰፋ ድሪባም ሆነ ሌላ ኦነጋዊ የሚደርበው ካባ አይደለም። ያም ሆኖ ለኦሮሞ ብሔርተኞች እውነት፣ ታሪክና እውቀት ትርጉም ስለሌላቸው ዶክተር አሰፋ ድሪባም አበበን ኦሮሞ ለማድረግ ያቀረበው አንዳች ተጨማጭ ማስረጃ የለም። ዐቢይ አሕመድ መርቆ በከፈተው የሰላሌ ኦሮሞ ባሕል ማዕከል ውስጥ አበበ ቢቄላ ኦሮሞ ተደርጎ ስሙ የተጠራው ይህንን የዶክተር አሰፋን አበበን ኦሮሞ የማድረግ እንቅስቃሴ ተከትሎ ነው።
የአበበ ቢቄላን እውነተኛ ማንነትና ታሪክ ልጁ ጽጌ አበበ መጽሐፍ ጽፋ ነግራናለች። መጽሐፉም በእጄ ይገኛል። መጽሐፉ እ.ኤ.አ. በ1996 ዓ.ም. በእንግሊዝኛ ቋንቋ የታተመ ሲሆን ርዕሱ “Triumph and tragedy: A history of Abebe Bikila and his marathon career» By: Tsige Abebe ይሰኛል።
የአበበ ቢቂላ ልጅ ጽጌ አበበ ስለ አባቷ ታሪክ ባሳተመችው መጽሐፏ እንደነገረችን የአበበ እናት የመዝን ተወላጅና የቄስ ልጅ የሆኑት ወይዘሮ ውድነሽ ሲሆኑ በሕይወት ዘመናቸው ሶስት ባሎችን አግብተዋል። የመጀመሪያው ባላቸው ቢቂላ ይባላሉ። ወይዘሮ ውድነሽ ከአቶ ቢቂላ የመጀመሪያ ልጃቸውን ኮሎኔል ክንፈ ቢቂላን ወልደዋል። ኮሎኔል ክንፈ የክቡር ዘበኛ አባል የነበረ ሲሆን አበበ ቢቂላን ክብሩ ዘመኛ እንዲቀጠር ያደረገው የአበበ የእናት ልጅ ነው። [ምንጭ: Tsige Abebe (1996)Triumph and tragedy: A history of Abebe Bikila and his marathon career, Page 6]
ወይዘሮ ውድነሽ አቶ ቢቂላን ፈትተው ሁለተኛ ባላቸውን አቶ ደምሴን አገቡ። ከአቶ ደምሴ አበበን ወለዱ። አበበን በወለዱ በሶስት ዓመቱ የአበበ አባት አቶ ደምሴ በእድሜ ወጣት ስለነበሩ እሳቸውን ፈትተዋቸው ሶስተኛ ባላቸውን
አቶ ተምትም ከፈለውን አገቡ። ጽጌ ያባቷን ታሪክ በጻፋችበት መጽሐፏ ስለዚህ ጉዳይ እንዲህ ትለናለች፤
“When he[Abebe] was three, his mother, Wudinesh Beneberu divorced Abebe’s father and married her third husband Temtime Kefelew. Wudinesh maintained that she divorced her second husband Demissie (Abebe’s father) because he was too young for her”. [ምንጭ ፡ Tsige Abebe(1996), Triumph and tragedy: A history of Abebe Bikila and his marathon career, Page 1]

ከዚህ ጽጌ አበበ ስለ አባቷ የጻፈችው ታሪክ የአበበ አባት አቶ ደምሴ እንደሆኑ በግልጽ ይታያል። አቶ ደምሴ የወይዘሮ ውድነሽ በነበሩ የትውልድ ቦታ የመዝን ሰው እንደሆኑም ጨምራ ጽፋለች።
ስለዚህ ቢቂላ የአበበ እናት የመጀመሪያ ባል እንጂ አበበ ከተወለደ በኋላ እናቱ ያገቡት የእንጀራ አባቱም አይደሉም። የአበበ እንጀራ አባት እናቱ ወይዘሮ ውድነሽ ሁለተኛ ባላቸውንና የአበበን አባት አቶ ደምሴን ፈትተው ያገቡት ሶስተኛው ባላቸው አቶ ተምተም ከፈለው ናቸው። አበበን እስከ ሰባት ዓመቱ ድረስ ያሳደጉትና አበበም ከአዲስ አበባ ወደ ጅሩ እየተመላለሰ ይጎበኛቸው የነበሩት የእንጀራ አባቱን አቶ ተምትም ከፈለውን እንደነበር ጽጌ አበበ ያባቷን ታሪክ በጻፈችበት መጽሐፏ ነግራናለች።

አበበ ደምሴ የአባቱ ስም ቢቂላ ተደርጎ እንዲጠራ የተደረገው አበበ ክቡር ዘመኛ ሲቀጠር እናቱ ከአበበ አባት በፊት ካገቡት ከመጀመሪያ ባላቸው ከአቶ ቢቂላ የወለዱት ወንድሙ ኮሎኔል ክንፈ ቢቂላ ክቡር ዘበኛ ሲያስቀጥረው “ወንድሜ ነው” ብሎ ሲያስመዘግበው ነው። ይህንንም የምትነግረን የአባቷን ታሪኩ የጻፈችው የአበበ ልጅ ጽጌ አበበ ናት። የአበበ ታሪክ ይህ ነው። ከዚህ ውጭ አበበና አቶ ቢቄላ የሚያገናኛቸው አንዳች የአባትና ልጅ ግንኙነት የለም። አቶ ቢቂላ የአበበ የእንጀራ አባት እንኳ አይደሉም።
እንግዲህ! የኦሮሞ ብሔርተኞች አትሌት አበበ ደምሴን የማያውቃቸው የቢቂላ ልጅ አድርገው ሙዚያም ውስጥ ኦሮሞ አድርገው ያስገቡት የአቶ ደምሴን ልጅ የለ አባቱ የቢቂላ ልጅ አድርገው ነው። ኦነጋውያን አበበ ደምሴን የማያውቃቸውና የእንጀራ አባቱ እንኳ ያሆኑት ሰው ልጅ አድርገው ኦሮሞነት አላብሰው የኦሮሞ ሙዚዬም ውስጥ ሲያስገቡት ልጆቹ፣ ቤተሰቦቹና ዘመዶቹ ምን ይሉን ይሆን የሚል ነገር አያስጨንቃቸውም። የፈጠራ ታሪካቸውም የሚጋለጥባቸው አይመስላቸውም።

የኦሮሞ ብሔርተኞች ፖለቲካ ሰማዩንም ምድሩንም «የኛ ነው» የሚል ወረራና መውረስ ስለሆነ የሚወሩትና የሚወርሱት እስካገኙ ድረስ ሌላው ሁሉ አያሳስባቸውም። ታላቁ አበበ ደምሴንም ኦሮሞ አድርገው ለመውረስ የፈለጉት የያዛቸው የማይለቀው የወረራና የመውረስ መንፈስ ይዟቸው እንጂ ኦሮሞ ጀግና አጥተው አይደለም። ነጭ ባሪያ አድርጎ የሸጠው አፍሪካዊ ጀግና ጀኔራል ጃገማ ኬሎ፣ ኢትዮጵን ድጋሜ ከወለዱት አባቶች ከቀዳሚዎቹ የሚሰለፈው ራስ ጎበና ዳጨ፣ የኢትዮጵያ የልማት አባቱ ጀኔራል ሙሉጌታ ቡሊ፣ ሐረርን፣ ባሌንና አርሲን ከዚያድ ባሬ፣ ከኦነግና ከኢሕአፓ ጋር ተዋግቶ የኢትዮጵያ ክፍል ሆኖ እንዲቆይ ያደረገው ጀኔራል መርዳሳ ሌሊሳ አይነት አገር አውልና ሀውልት ሊቆምላቸው የሚገቡ የኦሮሞ ተወላጅ አበኞችን አጥተው አይደለም።
ሆነው ግን የኦሮሞ ብሔርተኞች የተጠሩት ኢትዮጵያ ጠሎች ሆነው ስለሆነ ስለ ኢትዮጵያ ሟች የሆኑትን እነ ራስ ጎበናንና ጀኔራል ሙሉጌታን ማስታወስ አይሹም ፤ «ባሌና አርሲን ገሎጥዬ ከሃይማኖት ወንድሞቼ ከሶማሌዎች ጋር እዋሃዳለሁ» ብሎ ሞቃዲሾ የሸፈተውንና ለዚህም አላማው ዚያድ ባሬ የጄኔራልነት ማዕረግ ሰጥቶ በኢትዮጵያ ላይ ያሰማራውን ዋቆ ጉቱን በመማረክ ዘመቻውን ያከሸፈውንና ዋቆ ወደ ሶማሊያ ሪፑብሊክ ሊጠቀልላቸው የነበሩትን ባሌና አርሲ የታደገውን ጀኔራል ጃጋማን ማንሳት አይፈግሉም።

እነ ሰማዩም ምድሩም የኛ ውሸት ማምረታቸውን ወደፊትም ይቀጥላል! እኛ እንዲህ እየተከታተልን ውሸታቸውን ራቁቱን ማስቀረቱን እንቀጥላለን!
ከቻች የታተሙት ሶስት ገጾች የአበበ ቢቄላ ልጅ ስለ አባቷ ታሪክ ያሳተመችው መጽሐፍ ሽፋን፣ ስለ አበበ አባትና የእናቱ ሁለተኛ ባል ስለሆኑት ስለ አቶ ደምሴና ስለ አበበ እናት የመጀመሪያ ባል ስለ አቶ ቢቂላ የጻፈችውን ታሪክ የሚያሳዩ ናቸው።

አቻምየለህ ታምሩ

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s