አዲሱ የአባይ ድልድይ በአንድ ጊዜ 6 ተሽከርካሪዎችን እንዲያስተናግድ ሆኖ እንደሚሰራ ተገልጿል፡፡

የባሕር ዳሩ የአባይ ወንዝ ድልድይ 43 ሜትር የጎን ስፋት ኖሮት በአንድ ጊዜ 6 ተሽከርካሪዎችን እንዲያስተናግድ ሆኖ እንደሚሰራ ተገልጿል፡፡
የኢትዮጵያ መንገዶች ባለስልጣን ይፋ ባደረገው መረጃ እንዳሳወቀው ድልድዩ 380 ሜትር ርዝመት ይኖረዋል፡፡ በኢትዮጵያ እስካሁን ካሉት ድልድዮች በተለየ ዘመናዊ ሆኖ እንደሚገነባም ነው የገለጸው፡፡ ለአጠቃላይ ሥራውም የኢትዮጵያ መንግስት ከ1 ነጥብ 4 ቢሊዮን ብር በላይ እንደመደበ ባለስልጣኑ አስታውቋል፡፡

ድልድዩን ለመገንባት የውል ስምምነት የተፈራረመው ደግሞ የቻይና ኮሙኒኬሽን ኮንስትራክሽን ካምፓኒ (cccc) ነው፡፡
እንደ ባለስልጣኑ መረጃ ከነባሩ አባይ ድልድይ በ2 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ የሚገነባው አዲሱ የአባይ ወንዝ ድልድይ 43 ሜትር የጎን ስፋት ኖሮት በግራና በቀኝ በአንድ ጊዜ 6 ተሽከርካሪዎችን ማስተናገድ የሚችል ይሆናል፡፡

በውስጡ ባለ ሦስት መስመር የተሸከርካሪ መሄጃ ፣ የብስክሌት ተጠቃሚዎች መስመር እንዲሁም 5 ሜትር የእግረኛ መሄጃ እንደሚካትትም ነው የተገለጸው፡፡
ከድልድዩ ግንባታ ጎን ለጎን ተያያዥ የኮንክሪት ስትራክቸር ስራዎች፣ የተሽከርካሪ መወጣጫ፣ የትራፊክ ምልከቶች እና የድልድይ ላይ መብራቶች እንደሚኖሩትም ባለስልጣኑ አስታውቋል፡፡
የአባይ ወንዝ ድልድይን ለመገንባት ለተቋራጩ የ3 ዓመት የጊዜ ገደብ እንደተሰጠው የኢትዮጵያ መንገዶች ባለስልጣን ያወጣው መረጃ ያመላክታል፡፡

አብመድ

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s