ለድኅረ ምረቃ ትምህርት ፈላጊዎች በሙሉ

የጅማ ዩኒቨርሲቲ ለ2012ዓ.ም የትምህርት ዘመን በመደበኛው መርሐግብር በሁለተኛ እና ሦስተኛ ዲግሪ የተለያዩ የስልጠና ዘርፎች አመልካቾችን ተቀብሎ ማሠልጠን ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም የመማር ፍላጐት ያላችሁና የትምህርት ሚኒስቴርን የመግቢያ መስፈርት ማሟላት የምትችሉ አመልካቾች ከነሐሴ 06 እስከ ነሐሴ 17/2011ዓ.ም ድረስ በጂማ ዩኒቨርሲቲ ስልጠናዎቹ በሚሰጡባቸው ኮሌጆች በሚገኙ የኮሌጅ ሬጅስትራር ቢሮዎች በግንባር በመቅረብ መመዝገብ የምትችሉ መሆኑን ያስታውቃል፡፡

የማመልከቻ ጊዜ፤ ከ ነሐሴ 06 እስከ ነሐሴ

17/20 11 ዓ.ም. ድረስ
የመግቢያ ፈተና የሚሰጥበት ዕለት፤ አርብ (ነሐሴ 24/2011ዓ.ም)

የማመልከቻ መስፈርቶች

ለማመልከት የሚመጡ አመልካቾች ከዚህ በታች የተጠቀሱትን መስፈርቶች ማሟላት ይጠበቅባቸዋል ፡፡
በትምህርት መስኩ ወይም በተመሳሳይ የትምህርት መስክ የመጀመሪያ ዲግሪ ያለው/ያላት
ሁሉም አመልካቾች ከዋናው የት/ት ምዝገባ በፊት ከተመረቁበት ተቋም ኦፊሽያል ትራንስክሪኘት ወደ ጅማ ዩኒቨርሲቲ ሬጅስትራር እንዲላክላቸው ማድረግ አለባቸው ፡፡
በመንግስት ስፖንሰር ት/ታቸውን ለሚከታተሉ አመልካቾች ለክልሎች በተሰጠው ኮታ ተወዳድረው ስማቸው በክልሉ ፐብሊክ ሰርቪስ እና ሰው ሀብት ልማት ቢሮ በኩል ለጅማ ዩኒቨርሲቲ ሊላክ ይገባል፡፡ የስፖንሰርሺፕ ደብዳቤውም በሚመለከተው ክልል/ፌደራል መስሪያ ቤት ተፈርሞ ሊቀርብ ይገባል፡፡ በወረዳዎች ተፈርመው የሚቀርቡ የስፖንሰርሺፕ ደብዳቤዎች ተቀባይነት የላቸውም፡፡
ማሳሰቢያ ፡ –

  1. በት/ት ሚኒስቴር ለተመደባችሁ እና ከተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች ለምትመጡ የድኅረ ምረቃ ት/ት አመልካቾች ምዝገባችሁም ሆነ የመግቢያ ፈተና የሚሰጥበት ቀን ከላይ በተጠቀሱት ቀናት በተመሳሳይ መሆኑን እንገልጻለን፡፡
  2. ሁሉም አመልካቾች ዋናውን የትምህርት ማስረጃ ከማይመለስ ሁለት ኮፒና ሁለት ጉርድ ፎቶ ግራፍ ይዘው መቅረብ ይጠበቅባቸዋል ፡፡

ለተጨማሪ መረጃ የዩኒቨርሲቲውን ድረ-ገጽ http://www.ju.edu.et መመልከት ይቻላል ፡፡

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s