የምክትል ከንቲባ ታከለ ኡማ ጉዳይ ሐሰተኛ ዜና ወይስ የተቀለበሰ ውሳኔ?

በዚህ ሳምንት መጀሪያ የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ ታከለ ኡማ (ኢንጂነር) ከኃላፊነታቸው እንዲነሱ መወሰኑና በምትካቸው ሌላ ሰው ሊሾም መሆኑ ተሰምቶ ነበር።

ይህ ወሬ ግን ሐሙስ ዕለት የከንቲባው ጽህፈት ቤት “ከንቲባው በሥራ ላይ ናቸው” በማለት ከሥልጣን አለመነሳታቸውን በመግለጽ ወሬውን ‘ሐሰት ነው’ ሲል አጣጥሎታል።

ባለፉት ቀናት የተለያዩ መገናኛ ብዙኀን ከዚህ ጉዳይ ጋር ቅርበት አለን የሚሉ አካላትን አናገርን በማለት ሲዘግቡ የሚመለከተው የመንግሥት አካል ግን ምንም አስተያየት ከመስጠት ተቆጥቦ ቆይቶ ነበር።

ቢቢሲ ኦሮምኛ በዚህ ጉዳይ ላይ በቂ መረጃ ካላቸው ሰዎች አጣርቶ ምክትል ከንቲባው ከኃላፊነታቸው ሊነሱ መሆኑ “እውነተኛ እንደሆነ” ዘግቦ ነበር።

በወቅቱ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አካባቢ ያሉ መረጃዎችን መሰረት አድርጎ ለሚናገር ማንኛውም ግለሰብ፤ የኦዲፒ ማዕከላዊ ኮሚቴ ለሁለት ቀናት ያካሄደውን ስብሰባውን እስከ አጠናቀቀበት ድረስ ጉዳዩ ያለቀለት ይመስል ነበር።

ሐሙስ ዕለት አመሻሽ ላይ የኦሮሞ ዲሞክራቲክ ፓርቲ (ኦዲፒ) ለሁለት ቀናት ያካሄደውን ስብሰባ ማጠናቀቁ በተገለፀ በጥቂት ሰዓት ውስጥ የከተማ አስተዳደሩ ዝምታውን በመስበር “ኢንጂነር ታከለ ኡማ ሥራ ላይ ናቸው፣ ከሥልጠጣናቸው ተነስተዋል ተብሎ የወጣው ወሬ ስህተት ነው” በማለት በማህበራዊ መገናኛ ገፁ ላይ አስፍሯል።

ይህ መረጃ የወጣው የኦዲፒ ስብሰባ መጠናቀቁን ተከትሎ የኦዲፒ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ አዲሱ አረጋ የስብሰባውን መጠናቀቅ በፌስቡክ ገጻቸው ላይ ከገለጹ ከአንድ ሰዓት በኋላ ነው።

ቢቢሲ ኦሮምኛ ያገኛቸው መረጃዎች እንደሚያሳዩት ምክትል ከንቲባው ከስልጣናቸው እንዲነሱ ከሳምንት ቀደም ብሎ ከበላይ ኃላፊዎች ጋር በመነገሩ ምክትል ከንቲባው አስቀድመው ይዘዋቸው የነበሩ ፕሮግራሞቻቸውን ሰርዘው ነበር።

ከኃላፊነታቸው ሊነሱ እንደነበር የሚያሳዩ መረጃዎች

ለአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ ታከለ ኡማ (ኢንጂነር) ከሥልጣን መነሳታቸውን የሚገልፅ ምንም አይነት ደብዳቤ እጃቸው ላይ እንዳልደረሰ በዚህ ጉዳይ ላይ ቅርብ የሆኑ ሰዎችን በመጠየቅ ለማረጋገጥ ችለናል።

ይሁን እንጂ ጥቅምት 8 በፊት ምክትል ከንቲባው “በእጆችህ ላይ ያሉትን ሥራዎች አጠናቅቀህ ጨርስ፤ ሌላ ሠው ያንተን ቦታ ይተካል” ተብሎ ተነግሯቸው እንደነበር ለጉዳዩ ቅርበት ካነጋገርናቸው ሰዎች መካከል አንዱ ይገልጻሉ።

ኢንጂነር ታከለ ኡማ ከኃላፊነታቸው መነሳት እንደማይፈልጉና ይህም ጉዳይ ለእርሳቸው ከተገለጸላቸው በኋላ ደስተኛ እንዳልነበሩ፣ በሥራቸውም ላይ ጫና ፈጥሮ እንደነበር በሥራ አጋጣሚ ለእርሳቸው ቅርበት ያላቸው ሰዎች ለቢቢሲ ተናግረዋል።

ባለፈው ማክሰኞ የአድዋ ማዕከል ግንባታ ፕሮጀክትን ጨምሮ ሌሎች ሥራዎችን እያስመረቁና እያስጀመሩ መቆየታቸው ለዚህ ሌላው ማሳያ ነው የሚሉት እኚህ ግለሰብ የተለያዩ አካላት ‘በአንድ ጊዜ ይህንን ሁሉ ሥራዎች ለመስራት ለምን ተጣደፉ?’ ብለው ሲጠይቁ እንደነበር መረዳት ችለናል።

……Continue reading at

https://www.bbc.com/amharic/50093604

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s