የሳይኮሎጂው ፕሮፌሰር ገጠመኝ

የሳይኮሎጂ ፕሮፌሰሩ ወደ ክፍል ገብቶ የእለቱን ወሳኝ ትምርት ለመጀመር ወደ ቦርድ እንደዞረ ፉጨት ሰማ። ወደ ተማሪዎቹ ዞሮ ማን እንዳፏጨ ጠየቀቃቸው ፣ሁሉም ዝም አሉ።
ፕሮፊሰሩ ተረጋግቶ ፣ እስክሪቢቶውን ወደ ኪሱ እየከተተ ፣ የዛሬው ሌክቸር እዚ ላይ ያበቃል፣ አለና ፈገግ ብሎ ነገር ግን መጀመሪያ አንድ ታሪክ እነግራችኋለው አላቸው። ሁሉም በጉጉት መጠበቅ ጀመረ
” ትላንት ቤቴ እንቅልፍ ስላስቸገረኝ ፣ዝም ብዬ ተነስቼ ነዳጅ ሞልቼ በዛውም ልናፈስ ለዛሬም ጊዜ ለመቆጠብ ከመሽ ወጣሁ ነዳጅ ከሞላሁ በኋላ ከትራፌክ ነጻ የሆነው መንገድ ላይ እየተንሸራሸርኩ ከሆነ ድግስ ቦታ የወጣች የምትመስል ቆንጂዬ ወጣት አየሁ።
መኪናዬን አዙሬ እርዳታ እንደምትፈልግ ጠየኳት “ታክሲ እንዳጣች እና ቤቷ እንዳደርሳት ጠየቀችኝ”
ጋቢና ገባች….ማውራት ጀመርን….ውበት ብቻ ሳይሆን ባወራነው ርእስ ሁሉ በጣም ስማርት ጭንቅላት እንዳላት ከምታወራው መገመት ቻልኩ።
ቤቷ እንደደረስን ፣በጣም ጥሩ ሰው እንደሆንኩ ነገረችኝ ፣እኔም ጥሩ አስተሳሰብ እንዳላት ነግሬያት በሌላ ጊዜ ተገናኝተን ሻይ ቡና እንድንል ጠየኳት በሀሳቤም ተስማማች ፣ዩኒቨርስቲ ፕሮፌሰር እንደሆንኩ አውርተን ፣ስልክ ተለዋወጥን።
ልንለያይ ስንል አንድ ነገር ላስቸግርህ ስትለኝ ፣ምንም ችግር የለውም አልኳት ።”ወንድሜ አንተ የምታስተምርበት ዩኒቨርስቲ ውስጥ ተማሪ ነው፣ በኛ ግንኙነት እንዳይጎዳ ቃል ግባልኝ” አለችኝ ….ችግር የለም ብዬ ስሙን ጠየኳት ስሙንም ነገረችኝ።
ምናልባት ብዙ ተማሪዎች በዩኒቨርስቲው ውስጥ ስለሚማሩና ተመሳሳይ ስም ሊኖራቸው ስለሚችል ወንድምሽን እንዴት ልለየው እችላለሁ ? ስል ጠየኳት።
እሷም :- ወንድሜ አንድ መለያ ባህሪ አለው በሱ ታውቀዋለህ፣ ፉጨት ማፏጨት ያዘወትራል። አለችኝ
ከዛ ሁሉም ተማሪ ወደ አፏጨው ልጅ ዞሮ ማየት ጀመረ
ፕሮፌሰሩም :- “የሳይኮሎጂ PHDዬን ተምሬ እንጂ ገዝቼ አይደለም ያገኘውት ና ውጣ ብሎ ጆሮውን ይዞ ከክፍል አስወጣው… ይባላል

#ፍትሕ

Leave a comment